top of page
Writer's pictureGOD SPOT

መልካም እረኛ

የራሱንም ሁሉ ካወጣቸው በኋላ በፊታቸው ይሄዳል፥ በጎቹም ድምፁን ያውቃሉና ይከተሉታል፤ ከሌላው ግን ይሸሻሉ እንጂ አይከተሉትም፥ የሌሎችን ድምፅ አያውቁምና። ዮሐንስ 10 ¯⁴ -⁵

እየሱስ እረኛችን ነው ስለሆነም እንከተለዋለን ይህን የምናረገው ድምፁን ስለምናቀው ነው።ከላይ ከተፃፈው ሀሳብ ይሄን ነው የምንረዳው ነገር ግን የፅድቁን መንገድ ከመከተል ይልቅ በአለም ነገር ተጠላልፈን ራሳችንን እናገኛቸዋለን።እረኛውን የሚከተሉት በጎች የሚያውቁት ድምፅ የእረኝውን ብቻ ነዉ። ሰምተው ከህይወታቸው ጋር የሚያዋህድት የቃሉን እውነት ብቻ ነው።ከእረኛው ከተቀበሉት ሰማያዊዉ እውቀት እና ጥበብ ጋር ስለሚቃረን ሌሎች የጥብብ ድምፆች ለእነርሱ እንግዳ ናቸዉ።

ያዕቆብ 3: ¹³ -¹⁷ ¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯ ከእናንተ ጥበበኛና አስተዋይ ማን ነው? በመልካም አንዋዋሩ ስራውን በጥበብ የዋህነት ያሳይ። ነገር ግን መራራ ቅንዓትና አድመኛነት በልባችሁ ቢኖርባችሁ፥ አትመኩ በእውነትም ላይ አትዋሹ። ይህ ጥበብ ከላይ የሚወርድ አይደለም፤ ነገር ግን የምድር ነው፥ የሥጋም ነው፥ የአጋንንትም ነው፤ ቅንዓትና አድመኛነት ባሉበት ስፍራ በዚያ ሁከትና ክፉ ስራ ሁሉ አሉና። ላይኛይቱ ጥበብ ግን በመጀመሪያ ንጽሕት ናት፥ በኋላም ታራቂ፥ ገር፥ እሺ ባይ ምሕረትና በጎ ፍሬ የሞላባት፥ ጥርጥርና ግብዝነት የሌለባት ናት።

ታድያ ለምን ይሆን ከመንገድ ወጥተን በከንቱ የምንኳትነው? ምክንያቱም የህይወታችንን መሰረት ይሆን ዘንድ የምንከተለው የክርስቶስን ጥበብ ሳይሆን በዙሪያችን የሚነፍሱትንና በአንድ ጊዜ ወደ ሁሉም አቅጣጫ የሚመሩንን ነገር ግን የትም የማያደርሱንን ሀሳቦች ስለምንከተል ነው።

እየሱስ ግን መልካም እረኛ ነው እርሱን ብቻ ተከተሉት። "መልካም እረኛ እኔ ነኝ። መልካም እረኛ ነፍሱን ስለ በጎቹ ያኖራል። … መልካም እረኛ እኔ ነኝ፥ አብም እንደሚያውቀኝ እኔም አብን እንደማውቀው የራሴን በጎች አውቃለሁ የራሴም በጎች ያውቁኛል፤ ነፍሴንም ስለ በጎች አኖራለሁ።" ዮሐንስ 10:11,14-15


6 views0 comments

Recent Posts

See All

Comments


bottom of page