top of page

በድቅድቁ ጨለማ ውስጥ ብርሃንህን…

Writer's picture: GOD SPOTGOD SPOT

በዚህ ምድር ላይ ስንኖር ህይወት ሁለት ጽንፎች አሏዋት ጨለማ እና ብርሃን። የክርስትናን ሩጫ በእየለቱ ስንሮጥ

ሁሌም ምርጫ እንመርጣለን። ዘወትር በጨለማ እና በብርሃን መካከል የእኛን ልብ ለማሸነፍ የሚደረግ ፍልሚያ አለ እኛ

ደግሞ እንደ ክርስትያን ብርሃንን እንመርጣለን።ይሄ ምርጫችን ለህይወታችን ቅርጽን ያወጣለታል፤ክርስቶስን የሚመስል መልክ፤ ይሄ መልክ የሚመጣው ደግሞ በቅፅበት ሳይሆን በእለት ተለት ምርጫችን የሚወሰን ነው።


በእየሱስ ክርስቶስ በኩል ድነትን አግኝተን የእግዚያብሄር ልጆች ተብለን ብንጠራም በውስጣችን ያለው ጨለማው

ማንነት(ፍጥረታዊው ሰው) ከእኛ ውስጥ ሙሉ ለሙሉ አልተውገደም። ዘወትር ወደ እግዘያብሄር በቀረብን ቁጥር

ግን ይሄ ማንነት ከሚበራበት የእግዚያብሄር ቃል እውነት የተነሳ ጨለማው እየደበዘዘ ይመጣል።


ህይወታችንን እንደ አንድ መብራት እንደሌለው ባለ ብዙ ክፍል ቤት እናስበው።ዛሬ እግዚያብሄርን በመፈለግና ድምፁን

በመስማት ወደ እርሱ በተጠጋን ቁጥር አንድ አምፖል በአንዱ ክፍል ውስጠ እንደመግጠም ነው።ነገን ስንደግመው ደግሞ

በሌላኛው ክፍል እያለ የሚቀጥል የረጅም ጊዜ ጉዞ ነው።እርሱን ባወቅን ቁጥር የእውነቱ ብርሃን በህይወታችን ውስጥ ባሉ

ለማ ክፍሎች ላይ እያበራ የልጁ መልክ በእኛ ላይ ጎልቶ የታያል።

"በእርሱ ሕይወት ነበረች፥ ሕይወትም የሰው ብርሃን ነበረች።ብርሃንም በጨለማ ይበራል፥ ጨለማም አላሸነፈውም።" የዮሐንስ ወንጌል 1:4-5

“አቤቱ አባት ሆይ ብርሃንህ እስከውስጠኛው በህይወቴ የጨለመው ክፍል ድረስ አብዝቶ ይግባ።” አሜን!

15 views0 comments

Recent Posts

See All

Comments


bottom of page