top of page
Search

ከሁሉ በፊት...

  • Writer: GOD SPOT
    GOD SPOT
  • May 2
  • 1 min read

እርሱ አለምን ይሁን ብሎ ከመፍጠሩ በፊት ፣ ዓለም ብርሃንን ከማወቁ በፊት፣ እኔ በእግዚአብሔር ልብ ተሰውሬ ነበር። በዘላለማዊ ጸጥታ ውስጥ፣ ለመስራት የምጠባበቅ አንዲት  ሀሳብ ነበርኩ። እስትንፋሴ ሳይፈጠር፣ ስሜ ከመነገሩ በፊት፣ በአእምሮው ውስጥ እንዳለሁ ሳስብ  ልቤ  በትህትና የሞላል።

እንደዚህ የሚል አንድ  አስደናቂ ባዮሎጂያዊ እውነት አለ 'እያንዳንዱ ሴት ሲፈጠር ጀምሮ ሁሉንም እንቁላሎቿን የዛ ትወለዳለች.’ ይህም ማለት እናቴ በእናቷ ማህፀን ውስጥ በነበረችበት ጊዜ, አንድ ቀን እኔን የሚሆነው እንቁላል ቀድሞውኑ በእሷ ውስጥ ነበር የመጀመሪያ እስትንፋሴን ከመውሰዴ በፊት እንኳን የእርሷ አካል ነበርኩ - ከእርሷም በፊት የአያቴም አካል። የወደፊት ሕይወቴን የተሸከሙት ሴሎች ከመወለዴ ከረጅም ጊዜ በፊት አንድ ላይ ተጣምረው ነበር።

“በሆድ ሳልሠራህ አውቄሃለሁ፥ ከማኅፀንም ሳትወጣ ቀድሼሃለሁ፥ ለአሕዛብም ነቢይ አድርጌሃለሁ።” — ኤርምያስ 1:5

ይሄን ሁሉ ሳሰላስል መኖሬ ማለትም ሕይወቴ፣ ማንነቴ ከመወለዴ በፊት በአምላክ ዘንድ የታወቀ እንደነበር ተገነዘብኩ። የእኔ የመፈጠር ሂደት በዘፈቀደ ወይም በአጋጣሚ የሆነ ነገር አልነበረም። ህይወቴ የጀመረው የእናቴ የልብ ምት ከማስተጋባቱ በፊት ነው፣ ትንሹ እጄ በእጆቿ ከመያዙ በፊት አስቀድሞ አይቶኛል፣ ቀድሞውኑ ውዶኛል፣ ከሁሉም በፊት በእግዚአብሔር ተመርጬ ነበር።

ይህ እውነት እኔ በአጋጣሚ እንዳልሆንኩ ነገር ግን በፈጣሪዬ እጅ በጥንቃቄ የተሰራ መለኮታዊ ንድፍ አካል የመሆኔ ዘላለማዊ ማስታወሻ ነው። ከዘመናት መጀመሪያ በፊት በእግዚአብሔር ዘንድ መታወቄ ብቻ ሳይሆን የእኔ ማንነት ስነ-ህይወቴ ሁሉ እንኳን የእሱን ታላቅ ፍቅር ማሳያ ነው። ወደፊት እኔን የሚሆነው እንቁላል እኔ የምሆንበት ጊዜ እስኪደርስ ድረስ ተጠብቆ  በትውልዶች መካከል የተላለፈ ስጦታ ነበር



“ዓለም ሳይፈጠር፥ በፊቱ ቅዱሳንና ነውር የሌለን በፍቅር እንሆን ዘንድ በክርስቶስ መረጠን።” -ኤፌሶን 1፡4

በእግዚአብሔር ልብ ውስጥ ያለ ሃሳብ ነበርኩ፣ በእርሱ ፈቃድ ወደ መኖር የመጣ። ይህን ሳሰላስል ጥልቅ የሆነ ሰላም ይሰማኛል ውስጤም ሀሴት ያደርጋል። አልጠፋሁም ወይም አልተረሳሁም። እኔ ከማየው ወይም ከተረዳሁት እኔ ሙሉ በሙሉ ልረዳው ከምችለው በላይ እጅግ የላቀ ነገር አካል ነኝ። ስለዚህም በቀረው ዘመኔ ‘ብርሃን ይሁን’ ብሎ ከማወጁ በፊት እና ፀሀይ እና ከዋክብት ማብራትን ከመማራቸው በፊት የተወደድኩትንና የተመረጥኩ እንደሆንኩ የሚናገረውን እውነት ሸክሜ እጓዛለሁ።

 
 
 

Comments


bottom of page