የትንሳኤ በአል ውቅት በመሆኑ ከመቼውም ጊዜ በበለጠ የእየሱስ ክርስቶስን የመስቀል ስራ እናስባለን። በመስቀል ላይ
የክርስቶስ ደም መፍሰስ በእግዚያብሄር ዘንድ የራሱ አላማ ነበረው።
“ሰዎች ሁሉ ሊድኑና እውነቱን ወደ ማወቅ ሊደርሱ በሚወድ በእግዚአብሔር በመድኃኒታችን ፊት መልካምና ደስ የሚያሰኝ ይህ ነው።“ (1ኛ ወደ ጢሞቴዎስ 2፡3-4)
መልካሙን የፅድቅ መንገድ ትተን በክፋት እንዲሁም በራስ ወዳድነት በተሞላው የራሳችን መንገድ ሄድን። የዚህ
መንገድ እኔነት ነው ማለትም ለራሳችን ምኞትና ስጋዊ ተድላ መኖር ነው። የዚህ የሃጥያት መንገድ መጨርሻው ደግሞ ሞት
ነው። እግዚያብሄር ደግም የእኛን መሞት አይፈልግም።
”በውኑ ኃጢአተኛ ይሞት ዘንድ እፈቅዳለሁን? ይላል ጌታ እግዚአብሔር፤ ከመንገዱስ ይመለስና በሕይወት ይኖር ዘንድ አይደለምን?” (ትንቢተ ሕዝቅኤል 18:23)
በህይወት እንኖር ዘንድ ከራሳችን ሃጥያት መንገድ ተመልሰን በፅድቅ መንገድ እንጓዝ ዘንድ በዚህም ምክንያት በህይወት
“ኢየሱስም፦ እኔ መንገድና እውነት ሕይወትም ነኝ፤ በእኔ በቀር ወደ አብ የሚመጣ የለም። “ ተገለጠልን፡
“ኢየሱስም፦ እኔ መንገድና እውነት ሕይወትም ነኝ፤ በእኔ በቀር ወደ አብ የሚመጣ የለም። “ (የዮሐንስ ወንጌል 14፡6)
“የሕይወትን መንገድ አሳየኸኝ፤ ከፊትህ ጋር ደስታን አጠገብኸኝ፥ በቀኝህም የዘላለም ፍሥሐ አለ።” (መዝሙረ ዳዊት 16:11)
የህይወታችን ምንጭና መነሻ ራሱ እግዚያብሄር ነው ለዚህም ነው ከህይወታችን መሰረት ተለይተን በራሳችን መንገድ ስንሄድ
መጨረሻችርን ጥፋት የሚሆነው።ስለዚህ ይሄንን ህይወት መኖር የምንችለው ከእግዚያብሄር ጋር ስንጣበቅ ብቻ ነው።የዛፍ
ቅርንጫፎች ከግንድ ጋር በመጣበቅ በህይወት መቆየት እንደሚችሉ ሁሉ እኛም በህይወት ለመቆየት እየሱስ ያስፈልገናል።
የእኛ መንገድ በእኔነታችን የተሞላ እንደተሞላ ሁሉ የህይወት መንገድ ደግሞ ክርቶሳዊ/እግዚያብሄር ተኮር ነው።በዚህ
መንገድ ላይ ስንጓዝ የእያንዳንዱ ድርጊታችን አላማ ራሱ እግዚያብሄር ነው።
“እግዚአብሔር ጻድቅ ነውና፥ ጽድቅንም ይወድዳል፤ ቅንነት ግን ፊቱን ታየዋለች።” (መዝሙረ ዳዊት 11፡7)
ፅድቅ ደግሞ እግዚያብሄርን የመምስል ህይወት ነው። መፅሃፍ ቅዱስ ሲናገር እንዲህ ይላል። “ እግዚአብሔርንም የመምሰል
ምሥጢር ያለ ጥርጥር ታላቅ ነው፤ በሥጋ የተገለጠ፥ በመንፈስ የጸደቀ፥ ለመላእክት የታየ፥ በአሕዛብ የተሰበከ፥ በዓለም
የታመነ፥ በክብር ያረገ።” (1ኛ ወደ ጢሞቴዎስ 3:16) ይኧውም እየሱስ ክርስቶስ ነው። ይህን ህይውት እንዴት መኖር
እንዳለብን በዚህ ምድር ላይ በነበረበት ወቅት በህይወቱ በመኖር አሳይቶናል።
ትህትና- “ቀንበሬን በላያችሁ ተሸከሙ ከእኔም ተማሩ፥ እኔ የዋህ በልቤም ትሑት ነኝና፥ ለነፍሳችሁም ዕረፍት ታገኛላችሁ፤” (የማቴዎስ ወንጌል 11:29)
ፍቅር- “ኢየሱስም ከፋሲካ በዓል በፊት፥ ከዚህ ዓለም ወደ አብ የሚሄድበት ሰዓት እንደ ደረሰ አውቆ፥ በዚህ ዓለም ያሉትን ወገኖቹን የወደዳቸውን እስከ መጨረሻ ወደዳቸው።” (የዮሐንስ ወንጌል 13:1)
ትዕግስት- “በምስሉም እንደ ሰው ተገኝቶ ራሱን አዋረደ፥ ለሞትም ይኸውም የመስቀል ሞት እንኳ የታዘዘ ሆነ።” (ወደ ፊልጵስዩስ ሰዎች 2:8)…
እነዚህን ነገሮች እናድርግ ዘንድ በራሳችን አንችልም ይሄንንም እርሱ እግዚአብሔርም ስለሚያውቅ ፀጋውን ሰጠን።በራሳችን ደካማ ነን ለፅድቅ ከመኖር ይልቅ ለጥፋታችን እንሮጣለን።እግዚአብሔርም በልጅ በእየሱስ ክርስቶስ በኩል በፀጋው አዳነን።ይህም ፀጋ እግዚአብሔርን የመምሰል ፍፁም ሙላት እስክንደርስ ድረስ እንዲረዳን ከላይ ተሰቶናል።
Comments