top of page

የህይወት መገኛ እርሱ ነው

Writer's picture: GOD SPOTGOD SPOT

Updated: Apr 15, 2023

ማንነታችን እንዲሁም ሁለንተናቻን በእግዚአብሔር ላይ መሰረት ያደረገ ነው። እግዚአብሔር በመጀመሪያ ሰውን ሲፈጥር ህያው ሆኖ ከሌሎች ግዑዛን ነገሮች የተለየ ያደረገው እግዚአብሔር እፍ ያለበት የህይወት እስትንፋስ ነው።

“እግዚአብሔር አምላክም ሰውን ከምድር አፈር አበጀው፤ በአፍንጫውም የሕይወት እስትንፋስን እፍ አለበት ሰውም ሕያው ነፍስ ያለው ሆነ።” (ዘፍ 2:7)

እየሱስ ክርስቶስ በዮሃንስ ወንጌል ምዕራፍ 15 ላይ ሲነገር እርሱ የወይን ግንድ እንደሆነ እኛም ደግሞ ቅርንጫፎች እንደሆንን ከግንዱ ከተለየን በህይወት መኖር እንደማንችል እናገራል። ይሄ ክፍል እግዚአብሔር እና በእኛ በሰዎች መካከል ይለውን ጥብቅ ቁርኝት የምንመለከትበት ሌላኛው የመፅሃፍ ቅዱስ ክፍል ነው።

“እኔ የወይን ግንድ ነኝ እናንተም ቅርንጫፎች ናችሁ። ያለ እኔ ምንም ልታደርጉ አትችሉምና በእኔ የሚኖር እኔም በእርሱ፥ እርሱ ብዙ ፍሬ ያፈራል። በእኔ የማይኖር ቢሆን እንደ ቅርንጫፍ ወደ ውጭ ይጣላል ይደርቅማል፤ እነርሱንም ሰብስበው ወደ እሳት ይጥሉአቸዋል፥ ያቃጥሉአቸውማል።” (ዮሀ 15:5-6)

ሰው በህይወት ዘመኑ ሲኖር ከሚጠይቃቸው ጥያቄዎች አንዱና ትልቁ ጥያቄ ማንነትን ማወቅ እንዲሁም ራስን መረዳት የሚለው ሃሳብ ነው።ለዚህ ጥያቄ መልስ የሚሰጡ የሚመስሉ ብዙ ምንጮ በዚህ ምድር ላይ አሉ ነገር ግን አንዳቸውም እውነት አይደሉም። ዛሬ ከአንደኛው ያገኘነውንና እውነት ነው በለን የያዝንነውን እውቀት ነገ ሌላኛው ደግሞ ከንቱ ያረገዋል። እውነትን በተሳሳቱ ስፍራዎች እንፈልጋታለን ነገር ግን አናገኛትም ስለሆነም የእውነት ጥማችን ሳይረካ የቀራል ፡፡


የምንሰማው እውነት መሳይ መረጃዎች በሙሉ ተቀያያሪና ተለዋዋጭ ስለሆኑ በነዚህ መረጃዎች ላይ ህይወታችንን ስንመሰርት ያልተረጋጋና ከሚመጣውና ከሚሄደው ጋር ተላዋዋጭ ይሆነል። ከዚህም የተነሳ በህይወታቻን ውስጥ ያሉ ግንኙነቶች በጊዜና በሁኔታ ተቀያያሪ ናቸው::የምንወስናቸው ውሳኔዎች ቋሚነት የሌላቸውና አንድን ውሳኔ ከወሰንን በኋላ ፀሃይ ወጥታ ሳትጠልቅ ተፀፅተን ስንሽረው ራሳችንን እናገኝዋለን።


የእውነት መገኛ ከእግዚአብሔር ዘንድ ነው::ለእውነት ያለንን ጥማት ሊያረካልን የሚችለው እርሱ ብቻ ነው::ስለዚህ ወደ እግዚአብሔር እንመለስ፣ ወደ ቃሉ እንመለስ።እግዚአብሔር በማወቅ ውስጥ ብቻ ነው ራሳችንን ልናውቅ የምንችለው። ስለዚህ ለአፍታ ቆም ብለን እናስብ ህይወታችን ወዴት እያመራ ነው›? ስለዚህ ህይወታችንን ለማሳድግ ውሃ ይምንቀዳው ከየት ነው›? ከቃሉ ከሚፈልቀው የህይወት ምንጭ ነው ወይስ ጨዋማ ከሆኑት አለም ከምታቀርብልን ባሕራት ነው? እየሱስ በአንድ ወቅት ሲናገር እንደዚ ብሎ ነበር፦

“ኢየሱስም መልሶ፦ ከዚህ ውኃ የሚጠጣ ሁሉ እንደ ገና ይጠማል፤ እኔ ከምሰጠው ውኃ የሚጠጣ ሁሉ ግን ለዘላለም አይጠማም፥ እኔ የምሰጠው ውኃ በእርሱ ውስጥ ለዘላለም ሕይወት የሚፈልቅ የውኃ ምንጭ ይሆናል እንጂ አላት።” (ዮሐ 4:13-14)



እግዚአብሔርን ማወቅ የሁሉም ሚስጥር ቁልፍ ነው ስለዚህ አብዝተን እንቅረበው እንወቀው ሁለንተናችንን እናስገዛለት። ለእኔ ብለን የምናስቀረው ማንነት አይኑረን::የመኖራችን ትርጉም እርሱ ነው ስለዚህ የኑሮአችን መሰረት ቃሉ ይሁን።


“ስለዚህ ይህን ቃሌን ሰምቶ የሚያደርገው ሁሉ ቤቱን በዓለት ላይ የሠራ ልባም ሰውን ይመስላል።ዝናብም ወረደ ጎርፍም መጣ ነፋስም ነፈሰ ያንም ቤት ገፋው፥ በዓለት ላይም ስለ ተመሠረተ አልወደቀም።ይህንም ቃሌን ሰምቶ የማያደርገው ሰው ሁሉ ቤቱን በአሸዋ ላይ የሠራ ሰነፍ ሰውን ይመስላል። ዝናብም ወረደ ጎርፍም መጣ ነፋስም ነፈሰ ያንም ቤት መታው፥ ወደቀም፥ አወዳደቁም ታላቅ ሆነ።” (ማቴ 7:24-27)
20 views0 comments

Recent Posts

See All

Komentáře


bottom of page